ኮምፒዩተር

Article on other languages:

ኮምፒዩተር

ኮምፕዩተር ማለት ማንኛውም ኢንፎርሜሽን ፕሮሰስ የሚያረግ ማሽን ነው። ይህም የሚደረገው በተርታ የተቀመጡ ትዕዛዞች በመፈጸም ነው። ለብዙ ሰዎች ኮምፒዩተር ሲባል ዐዕምሯቸው ላይ የሚመጣው የግል (ፐርሰናል) ኮምፒዩተር ነው። ነገር ግን ኮምፒዩተር ሲባል በጣም ብዙ ነገሮችን ያጠዋልላል። ላፕቶፕ ፣ ዴስክቶፕ ፣ ምይክሮ-ኮምፒዩተር ፣ ሱፐር-ኮምፒዩተር ፣ ካልኩሌተር ፣ ዲጂታል ካሜራ አና ሌሎችንም ያጠቃልላል።

ይዞታ

ታሪክ

ቀድሞ ኮምፒዩተር ማለት አንድ በማቲማቲሺያን ትዕዛዝ የተለያዩ የጥንት መሣሪያዎችን እየተጠቀመ ቁጥሮችን የሚያሰላ ሰው ነበር። እስከ 20ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የተለያዩ ጠቃሚ መሣሪያዎች ተሰርተዋል። ከዛ በኋላ ትልልቅ ማሸኖች መሠራት ጀመሩ። እነዚህ ማሽኖች ከዛሬው ኮምፒዩተሮች ጋር ሲዋደሩ በጣም ታላቅና ቀርፋፋ ናቸው።

የኮምፒዩተር ዐይነቶች

ዋና የኮምፒየተር ዐይነቶች እንደሚከተለው ነው፦

  • ሱፐር-ኮምፒዩተር
  • ሜንፍሬም-ኮምፒዩተር
  • ዴስክቶፕ ኮምፒዩተር
  • ላፕቶፕ (ኖትቡክ)
  • ፓልምቶፕ

የኮምፕዩተር ክፍሎች

የኮምፕዩተር የውስጥ ክፍሎች የሚከተሉት ናቸው፡-



1.ሞኒተር(የምንሰራውን ነገር እንዲያሳየን፤ምስል፣ጽሑፍ ወይም ቪዲዮ ሊሆን ይችላል)

ሰኔ 16/2000

ሞኒተር 14 ኢንች 15 ኢንች.......እየተባለ ይገላጻል፡፡

14 ኢንች 15 ኢንች እያልን ስንናገር አለካኩ ከአንዱ ጎን ወደተቃራኒ ጎን በመለካት ነው፡፡(ስዕሉን ይመልከቱ፡፡)14 ኢንች 15 ኢንች እያልን ስንናገር አለካኩ ከአንዱ ጎን ወደተቃራኒ ጎን በመለካት ነው፡፡(ስዕሉን ይመልከቱ፡፡)

በፊት የነበሩት የላፕቶፕና ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች የሬሾ(ርዝመት ሲካፈል ለወርድ) 4በ3(በትክክል ሲጻፍ 4፡3 ይሆናል) ነበር፡፡

አሁን ደግሞ የቲያትር ሞድ የሚባለው ባለ 16፡9 ሬሾ ወይም ዋይድ ስክሪን (ws) በመጠቀም ላይ ናቸው፡፡



2.ማዘርቦርድ(እናት ቦርድ)(ሁሉም የኮምፕዩተር ክፍሎች(ዕቃዎች) የሚቀዳጁበት)

3.ሲፒዩ( የኮምፕዩተሩ አእማሮ እንደማለት ነው፡፡ይህ ሲባል ግን ሲፒዩን ከሰው አእማሮ ጋር አንድ ነው ማለት አይቻልም፡፡ )

4.ሜሞሪ(ማስታወሻ)( ዲስክ(የምንሰራውን ወይም የምንጠቀምበትን ፋይል በጊዚያዊነት ለማስቀመጥ)

ሰኔ 17/2000

ሜሞሪ(ማስታወሻ) በ Bytes ይለካል፡፡ከ Bytes ፊት Killo[1000 Bytes ማለት ነው፡፡ ] ፣ Mega[1,000,000 Bytes ] ፣

Giga[1,000,000,000 Bytes ] ወዘተ የሚሉትን ቃላት በመጠቀም Killo Mega፣ Mega Byte፣ Giga Byte

እያልን የኮምፒዩተር ሜሞሪ መተን እንገልጻለን፡፡

ለምሳሌ 10 MegaBytes ወይም ባጭሩ ሲጸፍ 10MB ይህ ማለት 10,000,000 Bytes ይሆናል ማለት ነው፡፡


5.ኤክስፓንሽ ስሎት

6.የኤሌትሪክ ሐይል(power supply)

7.የሲዲ ማሰሪያ(cd drive)

8.ሀርድ ዲስክ(የምንሰራውን ወይም የምንጠቀምበትን ፋይል በቋሚነት ለማስቀመጥ)

9.አቅጣጫ መጠቆሚያ(ማውስ)

10.የፊደል መምቻ(ኪቦርድ)

ዊኪፒዲያ ላይ ያለውን ምስል ከቁጥሩ ጋር ማነጻጸር ይቻላል፡፡

ኮምፕዩተሮች እንዴት እንደሚሰሩ

ታዋቂ ዋናዋና የኮምፕዩተር አምራቾች

ታዋቂ የኮምፕዩተር አምራቾች የሚከተሉት ናቸው፡፡ይህ ማለት ግን እያንዳዱን የኮምፕዩተር ክፍል(ዕቃዎች) ይሠራሉ ማለት አይደለም፡፡

1.አይቢኤም[IBM](አሁን እንኳ የፒሲ ክፍሉን እ.ኤ.አ. በ2004 ለቻይናው ሊኖቮ ሸጦታል)፡፡አሁን ሜን ፍሬም[Main Frame] ኮምፒዩተር ነው በብዛት የሚያመርቱት/የሚሠሩት፡፡

ድህረ ገጽ---[ http://www.ibm.com የአይቢኤም ድረ ገጽ ]

2.ዴል[Dell]

ድህረ ገጽ---[ http://www.dell.com የዴል ድረ ገጽ]

በኢትዮጵያ የዴል ወኪል አልታ ኮምፒዩተር ነው፡፡አድራሻቸው ቦሌ መንገድ ሸዋ ሱፐርማርኬት ፊትለፊት ነው፡፡ኔጃት ኮምፒዩተር ያለበት ፎቅ ነው፡፡

3.ኤሰር[Acer]

ድህረ ገጽ---[ http://www.acer.com የኤሰር ድረ ገጽ]

በኢትዮጵያ የኤሰር ወኪል ኔጃት ኮምፒዩተር ነው፡፡አድራሻቸው ቦሌ መንገድ ሸዋ ሱፐርማርኬት ፊትለፊት ነው፡፡አልታ ኮምፒዩተር ያለበት ፎቅ ነው፡፡

4.ቶሺባ [Toshiba]

ድህረ ገጽ---[ http://www.toshiba.com የቶሺባ ድረ ገጽ]


5. አፕል [Apple]

ድህረ ገጽ---[ http://www.apple.com የአፕል ድረ ገጽ]

6.ኤችፒ[HP]

ድህረ ገጽ---[ http://www.hp.comድ የኤችፒ[ድረ ገጽ]

ኮምፕዩተሮችና የዓለም ፊደላት

የመጀመሪያቹ ኮምፕዩተሮች የሚሠሩት በእንግሊዝኛ ፊደል ብቻ ነበር። ቀስ በቀስ ግን የተለያዩ ኣገሮች ሊቃውንት በየራሳቸው ፊደላት እንዲሠሩ ኣደረጉ። ኮምፕዩተር በእያንዳንዱ የግዕዝ ፊደል፣ ኣኃዝና ምልክት እንዲሠራ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈጠረው ኢትዮጵያዊው ዶክተር ኣበራ ሞላ ነው። በቅርቡም አያንዳንዱ የግዕዝ ፊደል፣ ኣኃዝና ምልክት ዩኒኮድ የሚባል የዓለም ፊደላት መደብ ውስጥ መግባት ቀጥሏል።

This article is from Wikipedia. All text is available under the terms of the GNU Free Documentation License.