አንጎላ

Article on other languages:

የአንጎላ ሪፑብሊክ
የአንጎላ ሰንደቅ ዓላማ የአንጎላ አርማ
(የአንጎላ ሰንደቅ ዓላማ) (የአንጎላ አርማ)
የአንጎላመገኛ
ዋና ከተማ ሏንዳ
ብሔራዊ ቋንቋ(ዎች) ፖርቱጊዝ
መሪዎች
ፕሬዝዳንት
ጠቅላይ ሚኒስትር

ሆዜ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ
ፈርናንዶ ዳ ፓይዳድ ዶስ ሳንቶስ
የነጻነት ቀን ኅዳር 1 ቀን 1968
(Nov. 11, 1975 እ.ኤ.ኣ.)
የመሬት ስፋት
(ካሬ ኪ.ሜ.)
1,246,700 (ከዓለም 22ኛ)
የሕዝብ ብዛት
(በ2004)
10,978,552 (ከዓለም 71ኛ)
የገንዘብ ስም ክዋንዛ
ሰዓት ክልል UTC +1
የስልክ መግቢያ +244

አንጎላ፣ በይፋ የአንጎላ ሪፑብሊክ (ፖርቱጊዝ: República de Angolaኪኮንጎ: Repubilika ya Ngola) በደቡብ-ምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ስትሆን ከናሚቢያ ፣ ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ፣ እና ከዛምቢያ ጋር ድንበር ትጋራላች። በምዕራብ ጫፍ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ጋር ትገናኛለች። የፖርቹጋል ቅኝ-ተገዥ ነበረች። ነዳጅ እና አልማዝ ከተፈጥሮ ሀብቶቿ የሚመደቡ ናቸው። የአንጎላ የሕግ-አስፈጻሚ ፕሬዝዳንቱን ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና የሚኒስትሮች ካውንስሉን ያጠቃልላል። ሁሉም ሚኒስትሮችና ምክትል ሚኒስትሮች የሚኒስተሮች ካውንስሉን ሲሰሩ በየጊዜው እየተሰበሰቡ ስለተለያዩ የፖለቲካ ጉዳዮች ውሳኔ ይሰጣሉ። የአስራ ስምንቱ ክልሎች ከንቲባዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚመረጡት። በ1992 እ.ኤ.ኣ. የወጣ ሕገ-መንግስት የመንግስቱን አወቃቀር እና የዜጎችን መብትና ግዴታ ይዘረዝራል። ፕሬዝዳንቱ መንግሥቱ በ2006 እ.ኤ.ኣ. ምርጫ ለማድረግ ዕቅድ እነዳለው ገልጸዋል። ይህ ምርጫ ከ1992 አ.ኤ.ኣ. በኋላ የመጀመሪያው ምርጫ ነው የሚሆነው። አንጎላ ውስጥ ሶስት ዋና ብሔረሰቦች ይገኛሉ። ኦቪምቡንዱ 37% ፣ ኪምቡንዱ 25% ፣ እና ባኮንጎ 13%። ሌሎች ብሔረሰቦች ቾክዌ (ሉንዳ)፣ ጋንጉዌላ፣ ንሀኔካ-ሁምቤ፣ አምቦ፣ ሄሬሮ፣ እና ዢንዱንጋን ያጠቃልላሉ። በተጨማሪም ክልሶች (አውሮፓና አፍሪካዊ) 2% ይሆናሉ። ፖርቹጋሎች አንጎላዊ ካልሆኑ ሰዎች ብዙዎቹ ናቸው።

ታሪክ

ንግሥት ንዚንጋ ከሏንዳ አስተዳዳሪ ጋር የሰላም ስምምነት ስታደርግ፣ 1657 እ.ኤ.አ.

በአንጎላ መጀመሪያ የሠፈሩት የኮይሳን ሰዎች ነበሩ። በባንቱ ፍልሰቶች ጊዜ እነዚህ ሰዎች ወደ ደቡብ አንጎላ ሄዱ። በ1483 እ.ኤ.አ. ፖርቱጋሎች በኮንጎ ወንዝ አጠገብ ሠፈሩ። በ1575 እ.ኤ.አ. ፖርቱጋል ካቢንዳ ጋር በባሪያ ንግድ ላይ ያቶከረ ግዛት መሠረተች። በ16ኛው ክፍለ ዘመን፣ ፖርቱጋል የአንጎላ የባህር ጠረፍን ተቆጣጠረች። በተለያዩ ውሎችና ጦርነቶች የፖርቱጋል ቅኝ-ግዛት አንጎላ ተስፋፋ። የፖርቱጋል መመለሻ ጦርነትን ምክኒያት በማድረግ የደች ሪፕብሊክ ሏንዳን ከ1641 እስከ 1648 እ.ኤ.ኣ. ድረስ ተቆጣጠረች።

የቅኝ ግዛት ጊዜ

በ1648 እ.ኤ.ኣ. ፓርቱጋል ሏንዳን እንደገና ተቆጣጠርች። በ1650 እ.ኤ.አ. ደግሞ የተነጠቀችውን መሬት እንዳለ አስመለስች። በ1671 እ.ኤ.አ. ፑንጎ አንዶንጎ የሚባለው ቦታ ወደ ፖርቱጋል ቅኝ ግዛት ተጨመረ። ፖርቱጋል በ1670 እ.ኤ.አ. ኮንጎን እና በ1681 እ.ኤ.አ. ማታምባን ለመውረር ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም። በ1885 እ.ኤ.አ. የበርሊን ጉባኤ የፖርቱጋል ቅኝ-ግዛት ድንበርን ከወሰነ በኋላ፣ በብሪታኒያ እና ፖርቱጋል ጥረት በኩል የባቡር-መንገድ፣ እርሻና ማዕድን ተሻሻሉ። እስከ ሀያኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ አካባቢው ሙሉ በሙሉ በፖርቱጋል አልተመራም ነበር። በ1951 እ.ኤ.አ. ቅኝ ግዛቱ የባህር ማዶ ክፍለ-ሀገር ሆኖ ፖርቱጊዝ ምዕራብ አፍሪካ ተባለ። ፖርቱጋል አካባቢውን ወደ አምስት መቶ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ያህል ተኮጣጥራለች። ስለዚህም የአካባቢው ሕዝብ ነጻነት ለመውጣት ያለው ስሜት የተደበላለቀ ነበር።

የአመራር ክልሎች

ክልል የሕዝብ ብዛት የመሬት ስፋት (ካሬ ኪ.ሜ.) ዋና ከተማ
1. ቤንጎ 450,000 33,016 ካክሲቶ
2. ቤንጉዌላ 600,000 1,788 ቤንጉዌላ
3. ባኤ 800,000 70,314 ኩዊቶ
4. ካቢንዳ 300,000 7,283
5. ኩዋንዶ ኩባንጎ 140,000 199,049 ሜኖንጉዌ
6. ኩዋንዛ ኖርቴ 400,000 24,110 ንዳላንታንዶ
7. ኩዋንዛ ሱል 600,000 55,660 ሱምቤ
8. ኩኔን 200,000 87,342 ኦንዲጂቫ
9. ሁዋምቦ 1,000,000 34,270 ሁዋምቦ
10. ሁኺላ 700,000 75,002 ሉባንጎ
11. ሉዋንዳ 3,000,000 2,257 ሉዋንዳ
12. ሉንዳ ኖርቴ 103,000 103,000 ሉካፓ
13. ሉንዳ ሱል 125,000 77,637 ሳውሪሞ
14. ማላንጄ 850,000 97,602 ማላንጄ
15. ሞክሲኮ 230,000 223,023 ሉኼና
16. ናሚቤ 60,000 58,137 ናሚቤ
17. ዩጂ 800,000 58,698 ዩጂ
18. ዛየር 600,000 40,130 ምባንዛ ኮንጎ


This article is from Wikipedia. All text is available under the terms of the GNU Free Documentation License.